የተሸከርካሪ ሽያጭ እና ኢንሹራንስን ጨምሮ ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ማዕከል የሚሰጥ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡
የተሸከርካሪ ሽያጭ እና ኢንሹራንስን ጨምሮ ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ማዕከል የሚሰጥ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ሁሉ አቀፍ የተሸከርካሪ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል የሚሰጥ በ50 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ፕሮጀክት ፀድቆ ወደስራ ሊገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስትና የግል አጋርነት ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
ፕሮጀክቱ በመንግስት የግል አጋርነት የሚሰራ ሲሆን በተበታተነ መልኩ ሲሰጥ የነበረውን የተሸከርካሪ ሽያጭ፣ የባንክና ኢንሹራንስ፣ውል እንዲሁም ቦሎ ና የመሳሰሉትን የከተሸከርካሪ አገልግሎቶችን በአንድ መዓከል ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስትና የግል አጋርነት ፅ/ቤት የኮሚኒኬሽንና የአቅም ግንባታ ጉዳይዎችች ከፍተኛ አማካሪ ዋጋዬ ተስፋዬ ናቸው፡፡
Read MoreSource: Ahadu Radio@Ethiopianbusinessdaily